የፋኖ ሰራዊት ድሎች በጎጃም

የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰራዊት ላለፉት አምስት ተከታታይ ቀናት ባደረጋቸው ዘመቻዎች ወሳኝ ድል አስመዝግቧል

የአማራ ፋኖ በጎጃም ከነሀሴ አንድ እስከ አምስት 05/2016 ዓ .ም ያደረጋቸው አውደ ውጊያዎች አስመልክቶ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው መረጃውን ከግንባር አድርሷል።

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ፋኖ ዩሐንስ ከነሃሴ1/2016 ሲጀምር ጠላት ከሞጣ ወደ ጎንጅ ሲመጣ የ2ኛ ክፍለ ጦር መብረቁ ብርጌድ አስቴርዮና ማክሰኝት ላይ ሲረፈርፈው ውሏል ብሏል።

የቀኝ ጌታየ ንጉሴ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ከ3ቀን ፋሚያ በኋላ ከሊባኖስና ደንባ አስወጥቶ ወደ ደ/ማርቆስ አስገብቶታል ሲልም አክሏል።

5ኛ ክፍለ ጦር ደጃች አሰቦ ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ዘመነ ካሴ ሻለቃ ደግሞ ቡሬ ከፍ ከተማ በመግባት ጠላትን ርፍርፎታል ያለው መግለጫው አገዛዙ ደግሞ 45 የስርዓቱ ካድሬዎችን ለምን ፈርታችሁ ቢሮ ዘጋችሁ ብሎ እንዳሰራቸው ጠቁሟል።

ነህሴ 2/2016 ደግሞ 7ኛ  ክፍለ ጦር አድራጊት ብርጌድ የብርሃኑ ጁላን ሰራዊት የዳ ወንዝና ጋጎ ጫካ ላይ ለብልቦታል ያለው ቃል አቀባዩ ሙትና ቁስለኛውን ለማንሳት አካባቢው ላይ ያሉ እረኞችን በማስገደድ ከብትና ፍየሎችን ወደ ውጊው በማስወሰድ እንደሽፋን ተጠቅሞ ሬሳና ቁስለኛውን አንስቷል ሲልም አስረድቷል።

የ1ኛ ክፍለ ጦር ቦንበኛ ቡድን ባህር ዳር ከተማ ላይ ቀበሌ 1ቴሌ ጀርባ፣ 14 ጎርደማ ገብርኤል የአድማ ብተና ካምፕ ላይና ሌሎች የተጠኑ ቦታዎች ላይ ባደረገው ጥቃት በርከት ያሉ ካድሬና አድማ ብተናዎች ላይ እርምጃ መውሰዱም ተነግሯል።

1 ክፍለ ጦር ባህር ዳር ብርጌድ ደጉ በላይ ሻለቃና የጣናው መብረቅ ብርጌድ ቅንባባ ሻለቃ ቅንባባ ላይ ጠላት ከባህር ዳርና አዴት መጥቶ ጓዝ ለመቀባበል ቢሞክርም 2 ፓትሮል ሃይሉን መማረካቸውም ታውቋል።

ነሃሴ 3 /2016 ደግሞ የ1ኛ ክፍለ ጦር ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ አለማየሁ ከቤ ሻለቃና ሻለቃ መማር ጌትነት መራዊና ቻይና ካምፕ ላይ ጠላትን ረፍርፈው የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ማርከዋል ብሏል ቃል አቀባዩ።

5ኛ ክፍለ ጦር ጀግናው ገረመው ወንዳውክ እና አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ማክሰኛና አጤ ውሃ ላይ ጠላትን ልኩን አሳይተው መልሰውታል ያለው ቃል አቀባዩ ይሄ ውጊያ ትናንት ጨምሮ ገነት አቦ ላይ ትልቅ ትንቅንቅ እየተደረገበት ይገኛል ሲልም አክሏል።

የ5ኛ ክፍለ ጦር አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ፍኖተ ሰላም ከተማ ጫፍ ላይ ኬላ ላይ ባለው የጠላት ኃይል ላይ ባደረሱት መብረቃዊ ጥቃትም ወሳኝ ድል መቀዳጀት እንደቻለ ተገልጿል።

5 ክፍለ ጦር ስበር ወንበርማ ሻለቃ ወንበርማ ወረዳ ውስጥ ጎመርና ባና ላይ ለከበባ የመጣን  የጠላት ኃይል ልብልበው መልሰውታል ሲልም ቃል አቀባዩ ጨምሮ ገልጿል።

ነሀሴ 4/2016 5ኛ ክፍለ ጦር ደጃች አስቦ ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ቡሬ ከተማ በመግባት 11 የጠላት ኃይሎችን ላይመለሱ ሸኝቷቸዋል ያለው መግለጫው ትናንት ደግሞ የ1ኛ ክፍለ ጦር ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ ቆቀር ቀበሌ ላይና ባህር ዳር ብርጌድ ደጉ በላይ ሻለቃ ደብረ ማዊ ላይ ጠላትን በመረፍረፍ 9 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ማርከዋል።

በውጊው የዐቢይ ጦር 35 ሙትና 21 ቁስለኛ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አመላክቷል።

በተጨማሪም የ1ኛ ክፍለ ጦር የጣናው መብረቅ ብርጌድ ቅንባባ ሻለቃ ከባህር ዳር ወደ አዴት በመሄድ ላይ የነበረን የአብይን ጨፍጫፊ ቡድን ቅንባባ ላይ 3 መኪና ኃይል ሲደመሰስ 2 መኪና ሽፋን እየሰጠ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ባህር ዳር ገብቷል ተብሏል።

5ኛ ክፍለ ጦር ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ከሰከላ የመጣውን ጠላት አዳማ ላይ ሲቀጠቅጠው ውሎ 1 ፓትሮል ተማርኳል ያለው ቃል አቀባዩ የ2ኛ  ክፍለ ጦር ደጋ ዳሞት ብርጌድ ወደ ቋሪት ሲሄድ የነበረን የጠላት ኃይል ቆባውና ደፈር ላይ በመለብለብ አቁመውታል ሲልም የፋኖ አመራሩ ገልጿል።

የአውደ ውጊያ ዝርዝር መረጃውን የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ቃል አቀባይ ፋኖ ዩሐንስ አለማየሁ አድርሶናል።

0 Comments

Login to join the discussion