የአማራ ፋኖ በጎጃም ትግል

በጎጃም ግዛት የአማራ ፋኖ ሰራዊት በወሳኝ ድል የታጀቡ ዘመቻዎችን ማድረጉን ቀጥሏል

ሰሞኑን በጎጃም ግዛት እየተካሄደ ያለው ጠንካራ ዘመቻ ሲቀጥል ትናንት  ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ በአማራ ፋኖ በጎጃም የታወጀው ጠላትን ከቀጣናው የማፅዳት ልዩ ዘመቻ በርካታ ትግልና ትንቅንቆች ተደርገው አያሌ ድልና ጀብዱዎች ተመዝግበው ውለዋል። 

ከድጎ ፅዮን ተነስቶ ሲንቀሳቀስ በነበረው የአገዛዙ ኃይል ላይ በደፈጣ ጥቃት ሲመታ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ግድያና ዝርፊያ ፈፅሟል ተብሏል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም አንደኛ ክፍለ ጦር የባህርዳር ብርጌድ የበላይ ጠባቂ ፋኖ ማንችሎት እሱባለው የድርጅቱን መሪ ትዕዛዝና አፈጻጸም ጨምሮ በባህርዳር የተፈጸመው ጥቃት አስመልክቶ ለሮሃ በሰጠው ቃል ተከታዩን ብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰዴ ወረዳ ባለው የጮቄ ተራራ ቀጠና በተደረገው ትንቅንቅ ደግሞ የተፈራ ዳምጤ ክፍለጦር ብርጌዶች ከፍተኛ ምት አድርሰውበት ወደ ሞጣ እንዲሸሽ መደረጉን የተፈራ ዳምጤ ክፍለጦር የህዝብ ግንኙት አመራር ፋኖ እሱባለው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል። 

አገዛዙን አሁን ላይ በገባበት ሁሉ አፍኖ ለመብላት የጎጃምን ቀጣና መስመሮች ሁሉ ከአምቡላንስና ፈቃድ ከተሰጣቸው የፋኖ ተሽከርካሪዎች በስተቀር ምንም እንቅስቃሴ እንዳይኖር እግድ ተጥሎ ትግሉ መቀጣጠሉንም የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የሕዝብ ግንኙነት አመራር ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ መግለጹን ዘገባው አክሏል፡፡ 

የቋሪት ቀጠና ላይ ከፍተኛ ተጋድሎና ትንቅንቅ እያደረገ ቀናትን ያሳለፈው የገረመው ወንድ አወክ ብርጌድም ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጎ ወደ አዴትና ብር አዳማ መሸሹና በደረሰበት ምት ቁስለኛና ሙቱን ማንሳት ሳይችል በየ ማሳውና በየጋራና ሸንተረሩ ግርጌ እየጣለ መሄዱን የገረመው ወንዳወክ ብርጌድ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ በለጠ አብረሀም አስታውቋል። 

አገዛዙ በዚህ በዚህ ቀጣና በደረሰበት ምትም ቁጥሩ ቀላል የማይባለው ሀይል በሽሽት የሞላ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ማለቁንም ፋኖ በለጠ አክሏል፡፡ 

አገዛዙ በዚህ መስመር አንድ መናገር የማይችልን አቅመ ደካማ ነዲያን ሳይቀር እጅ፣ እግር፣ ምላሱንና ብልቱን ጭምር ቆራርጦ በበቀል መግደሉን ሰምተናል።

ሌላው አገዛዙ ከደረሰበት የልዩ ዘመቻው ምትና በትር ውስጥ የብአዴን መቀመጫ በሆነችው ባህርዳር ልዩ ኦፕሬሽን ተሰርቶ በአገዛዙ ኃይል ላይ ከፍተኛ ምት የተፈፀመበት ይጠቀሳል፡፡ 

የአማራ ፋኖ በጎጃም አንደኛ ክፍለጦር ባህርዳር ብርጌድ በከተማው በከተማዋ ባደረገው ልዩ ኦፕሬሽን ከባድ መሳሪያዎችንና ሰራዊቱን ሲያንቀሳቅስ በነበረ የአገዛዙ ተሽከርካሪ ላይ በብርጌዱ ስር ያለችው አሳምነው ሻለቃ ባደረገችው የደፈጣ ዲሽቃ ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷ ተሰምቷል። 

የአማራ ፋኖ በጎጃም አንደኛ ክፍለጦር የባህርዳር ብርጌድ ቃል አባይ ሀብታሙ የሱፍ ለኢትዮ 251 ሚዲያ በሰጠው ቃል በከተማዋ ከተፈፀመው ይህ ጥቃት ባሻገር በአራት ቦታዎችም ላይ የቦምብ ጥቃቶች ተፈፅመዋል ብሏል። 

አሁን በጎጃም መስመር የተጀመረው ይህ ጠላትን ሙሉ በሙሉ የማፅዳት ዘመቻም ከአማራ ህዝብ ጋር በመሰናሰል ለታላቅ ድልና ስኬት እንደሚበቃ የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ እምነታቸውን ገልጸዋል ሲል ዘገባው አክሏል፡፡

በጎጃም ከሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ጎን ለጎን የአመራሮች ውይይትና ምክክር ቀጥሏል፡፡

የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ሰብሳቢ እና የጦር አዛዡ ሻለቃ ዝናቡ እንዲሁም ዘመቻ መምሪያው መቶ አለቃ አበበን ጨምሮ ስራ አስፈጻሚ አመራሩ ፋኖ ስሜነህ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ።

ከ9ነኛ ክፍለጦር አመራሮችና ከአረንዛው ጎንቻ ብርጌድ አመራር፣ አባላትና ጥሪ ከተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ሰፊ ውይይት ማድረጉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion