ሁለቱ የመቀሌ አዳራሾች

ህወሓት ክልሉን ወደ ብጥብጥ ሊወስዱ ከሚችሉ ውሳኔዎች እንዲቆጠብ ተጠየቀ 

ከሰሞኑ በፓርቲው ሕጋዊ ሰውነት መመለስ እና ድርጅታዊ ጉባኤን በማካሄድ መካከል በህወሃት ዋና ሰዎች መካከል መከፋፈል መፈጠሩን ተከትሎ በክልሉ ውጥረት እንዲባባስ አድርጓል።

የሳልሳይ ወያኔ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ብርሀኔ አጽብሀ እየተመለከትን ያለው ነገር ህውሓት ከስህተት የማይማር እና ለህዝቡ ምንም ግድ እንደሌለው የሚያመላክት ነው ብለዋል።

“ችግሩ የሚጀምረው ከፕሪቶርያው ስምምነት በኋላ ማድረግ ከጀመረው የፓርቲ ግምገማ ነው፤ ባለፉት ሶስት አመታት በጦርነት ውስጥ የማቀቀ፣ የመልሶ ማቋቋም የህግ እና ስርአት መከበር፣ የፕሪቶርያውን ስምምነት በተገቢው ልክ ማስፈጸም፣ በጎረቤት ሀገራት የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለስ እና ሌሎች መሰረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ ሲገባው ድርጅቱ በቀጣይነቱ ላይ ለምምክር ከሶስት ወር በላይ አዳራሽ ዘግቶ ስብሰባ መጀመሩ ከስልጣኑ ያለፈ ለህዝብ እንደማይቆረቆር ማሳያ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ፓርቲው ባደረገው የግምገማ መድረክ ላይ ልዩነቶችን ከማጥበብ ይልቅ ከዛ በከፋ እንዲለያይ እና ቡድን እንዲመሰረት ያደረገው እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ብርሀኔ፤ ከጉባኤው በኋላ በጊዜያው አስተዳደሩ እና በእነ ዶክተር ደብረጽዮን መካከል ይታይ የነበረውን ልዩነት ለአብነት አንስተዋል።

ሌላኛው በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀው ፓርቲ ባይቶና ምክትል ሊቀመንበር ዮሴፍ በርኸ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሲመሰረት በህውሓት የበላይነት እንዲቋቋም መደረጉ፣ የሲቪል ማህበረሰብ አካላት እና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አለመወከላቸው ክልሉ አሁንም በአንድ ፓርቲ እሰጣ ገባ ችግር ውስጥ እንዲገኝ ያደረገው ነው ባይናቸው።

ምክትል ሊቀመንበሩ አክለውም ፓርቲው አሁን ላይ ለሁለት ተከፍሎ የሚወዛገብበት ጉዳይ የህጋዊ ሰውነት እና የጉባኤ አጀንዳ ሳይሆን፤ ስልጣንን ይዞ መቀጠል በሚፈልገው የጊዜያው አስተዳደሩ አባላት እና ከጦርነቱ ማቆም በኋላ ከስልጣን ተገፍተናል በሚሉ ወገኖች መካከል የሚደረግ እንደሆነ ይናገራሉ።

በመሆኑም ህወሃት ከዚህ ተግባሩ እንዲቆጠብ ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ “ሁሉም ትግራዋይ ወዴት እያመራን ነው ? ሲል ራሱን በራሱ በመጠየቅ የመፍትሄ ሃሳብ መስጠት ይገባዋል” ሲሉ  አቶ ጌታቸው ረዳ አሳስበዋል፡፡


በመቐለ ከተማ ዓለም አቀፍ የትግራይ ሙሁራን ማህበር ለ3 ቀናት ያዘጋጀው ትግራይ ክልልን መልሶ በማቋቋም ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

" ያለውን መድረክ በመገንዘብ የመፍትሄ ሃሳብ በማስቀመጥ የበኩሉን ሃላፊነት መወጣት አለበት " ሲሉም አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።

" የሙሁራኑ ውይይት ማንኛውም ፓለቲካዊ ልዩነት ይኑር ችላ መባል እና መታለፍ የሌለባቸውን በመያዝ እንዲጠሩ መስራት ይጠበቅበታል " ሲሉ አስገዝበዋል። 

ለ3 ቀናት ይቆያል በተባለው የውይይት መድረክ በርካታ ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ ፣ ውይይትም ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። 

ከመላው ኢትዮጵያ ጨምሮ ፥ ከአፍሪካ ፣ አሜሪካ ፣ አወሮፓና ልሎች የዓለም ክፍሎች የተጋበዙ የትግራይ ሙሁራን በውይይት መድረኩ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ በእነ ደብረጽዮን ቡድን በኩል እየተካሄደ ያለው የህወሃት ጉባኤ ዛሬ 4ኛ ቀኑን ይዟል፡፡ በዚህም በመቀሌ ውስጥ ባሉ ሁለት አዳራሾች ሁለት ተቀናቃኝ ሃይሎች ስብሰባና ጉባኤ እያካሄዱ ነው፡፡ ውጥረቱ ወዴት ያመራል የሚለውም እየተጠበቀ ነው

0 Comments

Login to join the discussion