የአማራ ፋኖ ወታደራዊ ተጋድሎ

በጎንደር፡ ጎጃምና ወሎ የተለያዩ ግንባሮች ውጊያዎች መቀጠላቸው ተነገረ 

በአራቱም የአማራ ክፍለ ግዛት የፋኖ ወታደራዊ ኃይል በአገዛዙ ቡድን ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል፡፡

የአማራ ፋኖ በጎንደር የዓውደ ውጊያ ውሎዎችን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ የሥርዓቱ አገልጋይ ጨፍጫፊ ሠራዊት በደቡባዊ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት አሳሩን እያዬ ይገኛል ብሏል። 

መረጃው ከትናንት በስቲያ ነሐሴ 25/2016 ዓ.ም ጀምሮ በፋርጣና ፎገራ ወረዳዎች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ መርህ አልባው የዐቢይ ሽፍታ ሠራዊትን ለወሬ ነጋሪ በሚያስቸግር መልኩ አርበኞቹ የአጼ ቴዎድሮስ የግብር ልጆች ሲወቁት ውለዋል ብሏል። 

በቅርቡ አለምበር ላይ በተቀናጀ ደፈጣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ወታደራዊ መኮንኖችንም እስከወዲያኛው የሸኙትንና ለከፍተኛ ቁስለት የዳረጉ የፋኖ አርበኞችን እበቀላለሁ በሚል ከበባ ለማድረግ ከደብረታቦር የተነሳው የዐቢይ ጦር ወድሟል፡፡

 የሥርዓቱን ወንበር ጠባቂ ሠራዊት በመጣበት እግሩ አለምበር ላይ አንደኛው ግንባር፣ ቦርሳ ማርያም ላይ ሁለተኛው ግንባር፣ ክሙል ላይ ሦስተኛው ግንባር እንዲሁም አሞራ ገደል ላይ አራተኛው ግንባር ላይ በጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን የፋኖ ጦር አስታውቋል፡፡

የአማራ ፋኖ በጎንደር ሜጀር ጄነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር፣ ጉና ክፍለ ጦርና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ጄኔራል ተገኝ ክፍለ ጦር በቅንጅት በርካታ የጠላት ኃይልን መደምሰሳቸውን ሮሃ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል፡፡

በወሎ ግዛት ደግሞ የአማራ ፋኖ በወሎ የመቅደላ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ይታገሱን መሰዋት ተከትሎ ድርጅቱ ዘመቻ አርበኛ ይታገሱ አራጋውን ማወጁን ተከትሎ በመላው ወሎ ግዛት ልዩ ዘመቻው ተጀምሯል፡፡

 አማራ ሳይንት ቀጠና ታቦር ብርጌድም ዘመቻውን በመከተል በአገዛዙ ሃይሎች ላይ ጠንካራ በትር አሳርፏል፡፡

 በዘመቻ አርበኛ ይታገሱ 1 መኪና ሙሉ በሙሉ ሚኒሻ እና ፖሊስ ከነመኪናው ሲቃጠሉ 1 መኪና ባንዳዎች ቁስለኛ ሆነው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል፡፡

ኢትዮ 251 እንደዘገበው ከሆነ በህክምና ላይ ካሉት የወረዳውን የፀጥታ ኃላፊውን ጨምሮ 9 ባንዳዎች እስከ ወዲያኛው የተሸኙ ሲሆን በዚሁ ኦፕሬሽን1ድሽቃ 1 ስናይፐር 3 ብሬን እና 18ክላሽ መማረክ እንደተቻለ ታውቋል፡፡


ወደ ጎጃም ግዛት ስንሻገር ደግሞ ቀናትን እያስቆጠረ በቀጠለው የደጋዳሞት ግንባር ውጊያ የአገዛዙ ኃይል መዳከሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከቀናት በፊት የአማራ ፋኖ በጎጃም ወታደራዎ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡን እንይዛለን በማለት ከደንበጫ አንድ ሻለቃ ጦር እና በቂ ሎጀስቲክ በመጨመር የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ 23ኛ ክፍለ ጦር ውጥኑ እንደከሸፈበት ይታወቃል፡፡

የብልጽግና እንቅስቃሴን ለማክሸፍ በመከላከል ላይ የነበረው የደጋዳሞት ህዝብ እና የደጋዳሞት ብርጌድ ከመከላከል ወደ ማጥቃት በመሸጋገር 2ብሬን ከ50በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲሁም በርካታ ተተኳሽ መማረክ ችለዋል። 

በዚህ ቀን በተጀመረው ጦርነት የተመታው ጠላት ከበላይ አለቆቹ ቁጣ የደረሰበት የብርሃኑ ጁላ ጦር አስክሬን እና ቁስለኛ ሳያነሳ በመውጣቱ እና ሻለቃ ዝናቡን ባለመያዛቸው የተበሳጨው ጠላት ድጋሚ የሚከፈለው ዋጋ  ተከፍሎ ተልኮውን ድጋሚ እንዲፈፅሙ ተጨማሪ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው እንደነበርም ተሰምቷል፡፡

ይሁን እንጂ የዳሞት አርበኛ ፋኖዎች ከመሪያቸው ትዕዛዝ  ተቀብለው ማጥቃት በማድረግ የጠላትን ሃይል ከጥቅም ውጭ አድርገዋል፡፡

 ትናንትም ከፋኖ ጀግኖች ጥይት የተረፈው ጠላት ተመልሶ ወደነበረበት ከተማ ገብቷል ተብሏል።

0 Comments

Login to join the discussion