በጎንደር ከተማ እየተፈፀመ ያለውን እገታ የብልፅግና ሰዎች እንደሚፈፅሙ የሚያረጋግጥ መረጃ ይፋ ሆነ

የጎንደር ከተማና አካባቢውን እገታ ከሚመሩት ዋነኞቹ የፖለቲካና ፀጥታ መዋቅሩ ውስጥ ያሉ ኃይሎች እንደሚፈፅሙት ይታወቃል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ራሱ የአማራ ብልፅግናም በመግለጫው አምኗል። ከ34 በላይ ወንጀለኞች መያዛቸው ይታወቃል።


አሁን በተረጋጠ መረጃ ባለፈው ሳምንት ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ማራኪ ክፍለ ከተማ  እናት ልጅ የተገደሉበት የእገታ ወንጀል የተመራው አወቀ ጫኔ በሚባል ትራፊክ  ፖሊስ ነው። 


በቅርቡ ከፖሊስ ወደ ትራፊክነት የተቀየረው ይህ ግለሰብ ጭምብል በመልበስ ወደ ወ/ሮ መብራት ኪዳነ ማርያም ቤት ከግብረ አብሮቹ ጋ በመግባት ለማገት ሲሞክር፣ ሟች ወ/ሮ መብራት ራሷን ለመከላከል ባደረገችው ጥረት በባለቤቷ ማካሮፍ አንደኛውን አጋች በመግደል፣ አንደኛውን በማቁሰል ታግላ ነበር። ሆኖም ግን በአወቀ ጫኔና  ግብረ አበሮቹ በተተኮሰባት ጥይት እሷ እና ልጇ ሕይወታቸው አልፏል።ይህን ወንጀል ሲከታተሉ የነበሩ የአካባቢው ሰዎች በተጨባጭ ያገኙት መረጃ የወንጀሉ መሪ ተዋናይ አወቀ ጫኔና ግብረ አበሮቹ እንደሆኑ ተረጋግጧል። ይህ ፖሊስ ሆኖ  ሲያገለግል የነበረው ግለሰብ በአሁኑ ሰዓት ትራፊክ ቢሆንም፣ ከከተማው ፖሊስ ኮሚሽነር አየልኝ ጋር ጥብቅ ወዳጅነት መስርቶ አብዛኛውን የእገታ ወንጀል በመምራት ላይ ይገኛል። አሁን በቁጥጥር ስር ውሏል።


ይህ ግለሰብ ዛሬ አካውንቱ ሲረጋገጥ   18,000,000  ብር ተገኝቶበታል። የዚህ ሰው ወርሃዊ ደመወዝ 7,500 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ) ብር እንደሆነ ይታወቃል። በአካውንቱ የተገኘው ብር ምንጩ በበርካታ እገታዎች ተሳትፎ ያካበተው እንደሆነ ተረጋግጧል። 


በእናት እና ልጅ የእገታ ግድያው ወቅት እሱ መሆኑ የተጋለጠው ጭንብ ለብሰው ለማገት ሲሞክሩ የሞቱ እናት እና ልጅ አንታገትም ብለው ሲታገሉ (እናትየዋ ራሷን ለመከላከል በመተኮሷ) አጋቾቹ ያደረጉት ጭንብል በመውለቁ ነው። 

በኋላም ሟቹን አጋች አስከሬን ጥለው፣ ቁስለኛውን ይዘው ሲሸሹ የአካባቢው ሰው ተመልክቷል። በጥቆማ ሊያዝ የቻለውም በዚህ ሁኔታ ነው። 


የከተማው ዘረፋ በተቀናጀ መንገድ ከላይ ሆኖ እየመራው ያለው ረ/ኮሚሽነር አየልኝ ይባላል። 


ኮሚሽነሩ  የደሳለኝ ጣሰው የቅርብ ሰው በመሆኑ የወንጀል ትስስሩ እስከ ክልሉ ካቢኔ ድረስ የተያያዘ ነው። 

እናት እና ልጇን የገደለው አወቀ ጫኔ የኮማንደር አየልኝ ቀኝ እጅ  ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች ከታሰረበት ሊያስፈታው ይችላል ሲሉ ይገልፃሉ። ይህን መረጃ የጎንደር ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መላ አማራ፣ ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያውቀው ይገባል ሲሉ ይጠይቃሉ።ይህ ሰው በገለልተኛ አካል ቢመረመር በርካታ የአገዛዙን ጉድ እንደሚያጋልጥ ምንጮች ያደረሱት መረጃ ያሳያል። ምን አልባት ይህን መረጃ አየር ላይ  በማዋላችን አወቀ ጫኔን እስር ቤት ውስጥ በመግደል መረጃ ሊያጠፉ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። 


በጎንደርና አካባቢው የሚፈፀመው የሰው እገታና ግድያ በአገዛዙ የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ባሉ ወንበዴዎች እንደሚፈፀም ሊታወቅ እንደሚገባውም ተጠቁሟል።

የጎንደር ወጣት ከፋኖ በቀረበልህ የትግል ጥሪ መሰረት የቻልክ ትግል ሜዳ ውረድ፤ ካልችልክ የራስህ፣ የቤተሰብህና የከተማህ ወታደር ሆነህ ተሰለፍ የሚል ጥሪም ቀርቧል።


የአወቀ ጫኔ እና የረዳት ኮሚሽነር አየልኝ የሲሲሊ ማፍያን የሚያስንቅ የወንጀል ኔትወርክን አገር እንዲያውቀውና ገለልተኛ አካል ተቋቁሞ እንዲመረምረው ተጠይቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የብልፅግናው አገዛዝ በዛሬው እለት በጎንደር ጠዳ ከተማ ላይ ለገበያ የወይን ህዝብ መጨፍጨፉ ተሰምቷል።በዚህም በርካታ ሰዎች አልቀዋል። በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃዎች እንደደረሱን ወደ እናንተ የምናቀርብ ይሆናል።

0 Comments

Login to join the discussion